መልእክት ለነዋሪዎች ።
 የጤና ጥበቃ ምኒስትር ጤና ካለ መኖር አለ ይላሉ 
በአሁኑ ሰአት እጅግ አደገኛ የሆነ ተላላፊ  (ኮሬና)  በማለት የሚታወቅ ቫይረስ እየተራባ ስለሆነ የጤና ጥበቃ ሚንስትር ጠበቅ ያለ ማሳሰቢያ ለህብረተሰቡ እያስተላለፋ ይገኛል ።ይህ ተላላፊ በሽታ በ12/2019 ዓ,ም ታወቀ መነሻውም (በቻይና )መሆኑ ታውቋል በዚህም የተነሳ ማነኛውም ነዋሪ ወደ ቻይና መሄድ እንደሌለበት የጤና ጥበቃ ሚንስትር አስታውቋል ከቻይና ቆይቶ ለሚመለስ ማንኛውም  ህብረተሰብ መምርመራ ማድረግ አለበት ። ምክንያቱም ይህ በሽታ  እንደጉንፋን በቀላሉ ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፍ ስለሆነ መጠንቀቅ ያስፈልጋል ምናልባት ቢሆንም ምልክቶች ያሳያል ።
ምልክቶቹም 
1_ ከባድ የሆነ የሰውነት ሙቀት ይለቃል 
2_ ሀይለኛ ሳልና የትንፋሽ ማጠር ያሳያል በዚህም የተነሳ እሰከ ሞት ያደርሳል ።
የተጠቀሱትን ምልክቶች ቢያሳዩ ቶሎ ብለን ወደ ህክምና ቦታ (ምዩን)  መሄድ ወይም በስልክ ደውሎ እርዳታ መቀበል ያስፈልጋል 
ይህ (ነጊፍ) ከባድ በመሆኑ መጠን የጤና ጥበቃ ሚንስቴር ጥብቅ የሆነ ማስጠንቀቂያ አስተላልፈዋል ።
እንግዲህ ፤ ጎረቤት ሲታማ  ለኔ ብለህ ስመማ እንደሚባለው ጥንቃቄ በተሞላበት ሀኔታ  ማሰብ ይኖርብናል

 *አሰቻለዉ ምላ* 
የመማክርት ሸንጎ አባልና የቅሊጣ ሹም


 *אסצילאו מולה*  ממונה תיק קליטה